በካምብሪጅ አሳታፊ የበጀት አመዳደብ

Participatory Budgeting (PB) የማህበረሰብ አባላት የህዝብ በጀትን ከፊል እንዴት ማዋል እንዳለባቸው በቀጥታ እንዲወስኑ ስልጣን የሚሰጥ ዲሞክራሲያዊ ሂደት ነው። Cambridge(ካምብሪጅ) ከተማ PB ነዋሪዎች በበጀት አወጣጥ እና በግንባታ ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉ እንደሚረዳቸው ተስፋ ያደርጋል። PB የሲቪክ ተሳትፎን እና የማህበረሰብ መነቃቃትን ለማስተዋወቅ ይረዳል ብለን እናምናለን። የከተማው ካፒታል ፕላን Cambridge (ካምብሪጅ) ነዋሪዎችን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች የሚያንፀባርቅ መሆኑን ለማረጋገጥ እንፈልጋለን። 

ዘጠነኛው PB ዑደት ተጀምሯል፣ እና ከተማው Cambridge ለማሻሻል ስለ capital projects Cambridge ማህበረሰብ 1,000 በላይ ሀሳቦችን አሰባስቧል።   

ሃሳቦችን የመስጠት ቀነ-ገደብ አልፏል (ጁላይ 31) ሆኖም፣ ሃሳብዎን ወደ [email protected] ኢሜይል ከላኩ፣ በሚቀጥለው 10ኛው PB ዑደት ውስጥ እንደምናካትተው እርግጠኛ እንሆናለን። 

እባክዎትን ከዲሴምበር 1 ጀምሮ ይምጡ እና ሁሉም Cambridge ነዋሪዎች 12+ የዜግነት ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምን ድምጽ በሚሰጡበት እና ከከተማው ካፒታል በጀት 1 ሚሊዮን ዶላር እንዴት ማዋል እንዳለባቸው ይወስናሉ። 

ካለፉት PB ዑደቶች አሸናፊ የሆኑ ፕሮጀክቶች የወጣት ማእከል ማሻሻያዎችን፣ newly housed (አዲስ መኖሪያ ቤት ላሉ ነዋሪዎች) የቤት አቅርቦቶች፣ Main Library (ዋናው ቤተ-መጽሐፍት) የሶላር ፓናሎች፣ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች የልብስ ማጠቢያን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያካትታሉ!   

የክስተቶች የጊዜ ሰሌዳ፡-  

  • ጁን እና ጁላይ - ሃሳቦችዎን ያስገቡ!  
  • ከኦገስት እስከ ኖቬምበር - በጎ ፈቃደኞች እነዚያን ሀሳቦች ወደ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ያዘጋጃሉ። City Manager (ከተማው አስተዳዳሪ) እና የከተማው ሰራተኞች PB ድምጽ መስጫ ሀሳቦችን ያፀድቃሉ። 
  • ዲሴምበር - PB ድምጽ መስጠት! የዜግነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ሁሉም Cambridge ነዋሪዎች እድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ከሆነ ድምጽ መስጠት ይችላሉ። 

   Cambridge ውስጥ Participatory Budgeting (አሳታፊ በጀትን) ስለደገፉ እናመሰግናለን!